የምክር ቤቱ የፕሬስ እና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አዲስአለም እንቻለው ጉባኤውን በማስመልከት በሰጡት መግለጫ ምክር ቤቱ የፊታችን ቅዳሜ ሃምሌ 10 ቀን 2013 ዓ.ም በሚያካሂደው 8ኛ አመት 3ኛ መደበኛ ጉባኤው የተያዙ አጀንዳዎችን አብራርተዋል::
መደበኛ ጉባኤውም የ2013 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም የማጠቃለያ ሪፖርት ላይ እንደሚመክር ዳይሬክተሩ ገልጸዋል ።
በተጨማሪም የ2014 በጀትን ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም አቶ አዲስአለም ጠቁመዋል::
የአስተዳደሩ የኦዲት ግኝት ሪፖርትም ለምክር ቤት እንደሚቅርብና ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ ገልፀዋል::