የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን በመወከል በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በቤጂንግ ከተማ በመገኘት ከፉጃን ክፍለ ሀገር አመራሮች ጋር ተፈራርመዋል፡፡
መዲናችን አዲስ አበባ እና ፉጃን ክፍለሀገር የእህትማማች መመስረቻ ሰነድ በመፈራርማቸው ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል ያሉት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ እና በቻይና ህዝቦችና መንግስታት መካከል ያለውን ትስስር የበለጠ እንደሚያጠናክር እምነቴ የፀና ነዉ ብለዋል፡፡
በተጨማሪም በአዲስ አበባ እና በፉጃን ክፍለሀገር መካከል በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በግብርና፣ በባህል፣ ቱሪዝም፣ ትምህርት፣ ስፖርት እና በጤና መስክ ዙሪያ ላይ ልምድ ልውውጥና ትብብር ማድረግ ያስችላል ብለዋል ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፡፡
ዛሬ በቤጂንግ ከተማ የተፈረመው የእህትማማች ከተሞች መመስረቻ ሰነድም
የቻይና መንግስት በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ሁለገብ የልማት እንቅስቃሴ በመደገፍ እና በዓለምአቀፍ መድረኮች ከኢትዮጵያ ጎን በመሰለፍ የሀገራችን የምንጊዜም አጋር መሆኑን በተግባር ያስመሰከረ መሆኑን ምክትል ከንቲባዋ ጠቁመዋል፡፡