አቶ ጥራቱ በየነ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ‘መዲናችን አዲስ አበባም ሆነ ኢትዮጵያችን ከፍ ብላ እንድትታይ የወጣቶችም ሆነ የመላው ነዋሪዎች አስተዋፅኦ እጅግ ከፍተኛ ነው ብለዋል። ‘
ስፖርት ለአንድ አገር ሰላም፣ እድገትና ብልፅግና የማይተካ ሚና አለው ያሉት አቶ ጥራቱ በየነ ኢትዮጵያን ለመሰለ በማያቋርጥ የእድገትና ብልፅግና ጉዞ ላለ አገር ስፖርት አምራች ዜጋ ወጣት በመፍጠር ያለው ሚና ከፍተኛና የማይተካ ነው ሲሉም አስታውቀዋል።
በቦሌ ክፍለ ከተማ የዘጠና ቀን እቅድ ልዩ ድጋፍና ክትትል እያደረጉ ያሉት አቶ ጥራቱ በየነ ክፍለ ከተማው በሁሉም መስክ ሞዴል ሆኖ እንዲወጣ ወጣቶች በግንባር ቀደምነት በመሰለፍና መላው ነዋሪዎችን በማስተባበር የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ሊያደርጉ እንደሚገባም በአፅንኦት ገልፀዋል ።