የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ፣ በማታና በርቀት ትምህርት መርሐ ግብር ያስተማራቸውን ከ6 ሺህ 163 የቅድመ ምረቃና ድሕረ ምረቃ ተማሪዎችን በወዳጅነት አደባባይ እያስመረቀ ነው።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ እና የዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ፣የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወ/ሀና ፣ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ እንግዶችና የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት በመካሄድ ላይ ይገኛል።