ነገ ጳጉሜ 1 በአገልግሎት ቀን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና መስሪያ ቤት ይመረቃል::
የዋና መስሪያ ቤቱ ህንፃ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀ ሲሆን የሃገሪቱን የሲቪል ምዝገባ ስርዓት እና የዲጂታላይዜሽን ስራ የደረሰበትን ደረጃ ሊያሳይ በሚችል መልኩ በመጠናቀቁ በነገው ዕለት የሚመረቅ ይሆናል::
ከዋና መስርያ ቤት በተጨማሪ በ9 ክፍለ ከተሞች የሚገኙ 33 የኤጀንሲው የወረዳ ጽ/ቤቶች ሞዴል ተደርገው በመገንባታቸው ለአገልግሎት ክፍት ይሆናሉ::