መርሃ ግብሩን ያዘጋጀው የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ሲሆን ከሁሉም የአገሪቱ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የመጡ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ስራ አስፈጻሚ አባላት እንዲሁም የቦሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ተሳትፈውበታል፡፡
የከተማ ግብርና ንቅናቄ መርሃ ግብሩ እየተካሄደ ያለው “ምግቤን ከጓሮዬ” በሚል መሪ ቃል ሲሆን በመርሃ ግብሩ ላይ የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪል ማኅበራት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር አለሙ ስሜ እና የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለስ አለሙ ተገኝተዋል፡፡