የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በከተማዋ ከሚገኙ አንጋፋ አትሌቶች ፣ አሰልጣኞች ፣የክለቦች ደጋፊዎች ፣ የተለያዩ ስፖርት ፌዴሬሽኖች ስራ አስፈፃሚና ባለድርሻ አካላት ጋር በወቅታዊ ሀገራዊና ከተማ አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አካሂዷል ።
በውይይቱ መድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ እንደገለጹት እንደሀገር የተደቀነብንን ፈተና በአሸናፊነት ለመወጣት የከተማችን የስፖርት ቤተሰቦች ተደራጅተው የአካባቢያቸውን ሰላም እና ፀጥታ መጠበቅ ይኖርባቸዋል ብለዋል።
በስፖርት መድረክ ያሳያችሁትን የአሸናፊነት ወኔ ሀገራችን ኢትዮጵያን ለመታደግ በሚደረገው የህልውና ዘመቻ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የአሸባሪ ህወሓት የዘረኝነት ትርክት እና የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሳይበገሩ ሊፋለሙና እውነታውን ለዓለም ሊያሳውቁ እንደሚገባ ኃላፊው አመልክተዋል ።
በመድረኩ የተሳተፉት የስፖርት ቤተሰቦች በበኩላቸው በስፖርት ዓለም አሸናፊ ሆኖ ክብር የምንቀዳጀው ኢትዮጵያ ስትኖር ነው ፤ ከማንም በላይ ሀገራችንን በማስቀደም ማንኛውንም መስዕዋትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን ብለዋል።
ሀገራችንን ለማዳን ከጀግናው ሰራዊታችን ጎን በግንባር በመዝመት ፣ በደጀንነት ድጋፍ በማድረግና በምንሰራበት እና በምንኖርበት አካባቢ ሰላምን ለማስጠበቅ ሀላፊነታችንን እንወጣለን ሲሉ ቃል ገብተዋል ።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!