ዶክተር ዐቢይ አህመድ በባዕለ ሲመታቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት “በኢትዮጵያ ረጅም የአስተዳደር ዘመን ግልጽና ተዐማኒ ምርጫ በማድረግ ለዛሬው ቀን ስላደረሰን እንኳን ደስ አለን” ብለዋል፡፡
በተደረገው ምርጫ የተመዘገበው ድል ኢትዮጵውያን በአንድ ያሸነፍንበት ነው ብለዋል፡፡
ጀግኖችን ካፈራው ህዝባችን አብራክ በመፈጠሬ ሁሌም እንዲኮራ ከሚያደርጉኝ ነገሮች መካከል የህዝባችን ጽናት ፣አይበገሬነት እና አትንኩኝ ባይነት ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህዝባችን ቤትኛውም ዘመን የእናት ሀገር ጥቃት የሚያንገበግበው፤ ጠላት ሲመጣ የግል ቅሬታውን ወደጎን ብሎ ሀገርን የሚያስቀድም ያሳየ ነበር ብለዋል፡፡
የውስጥ ሽኩቻን እንዳይኖር በመነጋገርና በህብረ ብሄራዊነት አንድነት መስራት ይኖርብናል ያሉት ዶ/ር አብይ አህመድ ለዚህም ሁሉንም ሕብረተሰብ ክፍሎች ያካተተ የውይይት መድረኮች ይኖሩናል ብለዋል፡፡
ጠላት የሰሜን እዝ ሰራዊት ላይ ግፍ ፈጽሟል፣ ት/ቤት እና የጤና ተቋማትን እየዘረፈ ህጻናትና ንጹናንን ገድሏል ለዚህም በእብሪቱ ዋጋ አስከፍሎናል ሲሉ ተናግረዋል።
በዚህም ወደን ሳይሆን ተገደን ህልውና ወደ ማረጋገጥ የገባንበት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፤ይህም ከኢትዮጵያ ጠል ሀይሎች ጋር ብቻ የገባንበት የህግ ማስከበር ዘመቻ ነው ብለዋል።
የተሟላ አቅም ያለው የጸጥታና ደህንነት ሀይል እንገነባለንም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ በዲፕሎማሲውም የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ባከበረ መልኩ በፍቅር አብረውን ከሚሰሩት አካላት ጋር መድረኩ ሁሌም ክፍት ነው መሆኑን ጠቁመዋል ።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያውያን ከኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ባሻገር የራሳችን አቅም ማሳያና የህብረታችን ገመድ እንደሆነም ዶ/ር አብይ በንግግራቸው ገልጸዋል ።
መንግስት ቅድሚያ ሰጥቶ ከሚሰራቸው ስራዎች መካከል የኑሮ ውድነት ማሻሻል ዋነኛው ነው፤ለመጪው ትውልድ የተሸለች ሃገር ለማስረከብ ተደምረን የተሻለ ስራ እንሰራለን ብለዋል ።
በመጪው 5 አመታት ኢትዮጵያ የሚለው ስም ከአይበገሬነት የምናስተሳስርበት ጊዜ ይሆናል የኢትዮጵያ ሰንኮፋ የሚነቀልበትና ህብረብሄራዊነት የሚያብብበት ጊዜ እንደሚሆን ጠቅላይ ሚንስትሩ ገልጸዋል ።