የዘንድሮውን የሴቶች ቀን ስናከብር በማያመች ሁኔታ ውስጥ ሆነው በስነምግባር የታነፀና ሃገሩን የሚወድ ትውልድ ለመገንባት ዋጋ የከፈሉ፣ ሳይማሩ ለልጆቻቸው የእውቀት ፀዳል የፈነጠቁ ፣ እንደ ሻማ ቀልጠው ለልጆቻቸው ብርሃን የሆኑ እንዲሁም የተሰጣቸውን ሃላፊነት በአግባቡ በመወጣት ለትውልድ ህያው ምልክት እና ተምሳሌት የሆኑ መንፈሰ ጠንካራ ሴቶችን በማሰብ ነው::
የሴቶች ቀንን ስናከብር እለቱን ብቻ ሳይሆን በተለያየ ምክንያት ሴት እህቶቻችን ላይ የሚደርሰውን ጫና እና ጥቃት በመቃወም ፣ በመታገል እንዲሁም ከጎናቸው በመቆም ጭምር ሊሆን ይገባል::
ዛሬ ላይ ያለን ሴቶች የተጀመረውን የትውልድ ግንባታ ራዕይ በማስቀጠል በራሳቸው የሚተማመኑ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶችን በመፍጠር ጠንካራ መሰረት ያላት እና የሴቶች ዘርፈ ብዙ ተጠቃሚነት የተረጋገጠባት ሃገር ለመገንባት የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል::
በድጋሚ እንኳን ለሴቶች ቀን አደረሰን!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ