በመላው አዲስ አበባ የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሂዷል!!
በዛሬው እለት በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ተቋማት የ2015ዓ.ም የትምህርት ዘመንን ማስጀመሪያ መርሀ ግብር እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በዚህ የትምህርት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የተገኙት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም በትምህርት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር በ2014 በጀት አመት የተማሪ ውጤት ከማሻሻል አንፃር ከፍተኛ ስራዎች ሲሰሩ እንደነበር አስታውሰው ሀገራችን የትውልዱ ነች ያለ እዚህ ትውልድ ሀገር ልትቀጥልም ልትኖርም አትችልም ስለሆነም ተማሪው እንደ ተማሪነቱ ይች ሀገር የራሱ እንድትሆን ተማሪዎች ተግተው መማር እና መስራት እንዳለባቸው መክረዋል።