2015 ዓ.ም ከመላው የከተማችን ነዋሪ ጋር በጋራ እያቀድንና እየተወያየን ለጥያቄዎች ምላሽ እየሰጠን ከተማችንን ከፍ ለማድረግ በትጋት ሰርተን ስኬት የተጎናፀፍንበት እና ፈተናዎችን በጸናው ሕብረታችን ያለፍንበት ዓመት ነበር::
የረዳንና ያሳካልን ፈጣሪ ይመስገን!!!
በስራዎቻችን ሁሉ ከጎናችን ለተሰለፋችሁ የከተማችን ነዋሪዎች ፣ አመራሮች ፣ የመንግስት ሰራተኞች ፣ ልበ-ቀና ባለሀብቶች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ሁሉ አብረን ላሳካናቸው ስኬቶች ምስጋናችን ይድረሳችሁ፡፡
ለመቀበል በተዘጋጀነው 2016 ዓመት አዲስ ተስፋ የምንሰንቀበት ፣ አዳዲስ ውጥኖችን ለማሳካት የምንተጋበት ፣የጎደለው ሁሉ እንደ ህዳሴው ግድብ የሚሞላበት ፣ የማይቻል የሚመስለን ሁሉ እንደ ግድባችን ተችሎ ሃሴት የምናደርግበት እንዲሁም ሰላማችን እንደ ህዳሴው ግድብ ሞልቶ የሚፈስበት የለውጥ እና የስኬት ዓመት እንዲሆንልን እመኛለሁ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
መልካም አዲስ አመት!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ