ትላንትምሽት በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የግብፅ አቻውን 2 ለ 0 አሸነፈ።

ጎሎቹን በ21ኛው ደቂቃ ዳዋ ሁቴሳ በ40ኛው ደቂቃ ሽመልስ በቀለ አስቆጥረዋል።
በማላዊ ቢንጉ ብሔራዊ ስታዲየም በተደረገ የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድቡን ሁለተኛ ጨዋታ የግብጽ አቻውን አሸንፏል።
ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አለን