ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር ከ500 ሚሊየን በላይ ችግኝ መትከል ችላለች፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሁነቶች መከታተያ ክፍል (situation room) ባደረሱት መልዕክት ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ አሁኗ 12 ሰዓት ድረስ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከ500 ሚሊየን በላይ ችግኝ መትከል መቻሉን አስታውቀዋል፡፡