ኢትዮጵያ 4ኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች።
በኦሪገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶቾ 5ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር ጉዳፍ ፀጋይ ለኢትዮጵያ 4ኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘች። በውድድሩ ሌላኛዋ አትሌት ዳዊት ስዩም የነሀስ ሜዳሊያ አስገኝታለች። ለውጤቱ መገኘት የ10ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቷ ለተሰንበት ግደይ ከፍተኛውን የቡድን ስራ ሰርታ 5ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። ኬንያ ብር አግኝታለች