የ2015 የትምህርት ዘመን የትምህርት ማስጀመሪያ ኘርግራም በአቃቂ ቃሊቲ ሳሎ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተካሂዷል።
በትምህርት ማስጀመር ኘሮግራሙ የተገኙት ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ በአዲሱ አመት፣ በአዲስ ካሪኩለም መጀመሩን ገልፀዋል።
የተማረ አዕምሮ ተራራውን ሜዳ ያደርጋል ያሉት አቶ ጃንጥራር፣ አሁን እየፈተነን ያለው ሁኔታ የሚቀየረው ምክንያታዊ ትውልድ ሲፈጠር ብቻ ነው ብለዋል።
የአቃቂ ቃሊት ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አበራ ብሩ በበኩላቸው፣ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን በክፍለ ከተማው ባሉ 230 ትምህርት ቤቶች፣ 118 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ ተከናውኖ ወደ ተግባር ተገብቷል።