ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
ሕብረተሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ (ማስ ስፖርት) ከንቲባ አዳነችን ጨምሮ ሌሎችም የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተሳተፉበት በመስቀል አደባባይ ተደረገ
አዲስ አበባ የሰላምና የአብሮነት ከተማ በሚል መሪ ሃሳብ ሕብረተሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በስፋት በተሳተፉበት ሁኔታ በዛሬው ማለዳ በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በአካል ብቃት እንቅስቃሴው ላይ እንዳሉት አዲስ አበባ የሰላም ፣የፍቅር ፣የአብሮነትና የኢትያዊነት መገለጫ ከተማ ናት፡፡ በአብሮነታችን እናደርጋታለን!! ብለዋል
ሁላችንም በጋራ በያለንበት አካባቢ የሕብረተሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ልማድ በማድረግ አንድነታችንን ልናጠናክር ይገባል ብለዋል ከንቲባ አዳነች
እንደ ከንቲባ አዳነች አባባል እኛ ለአብሮነታችን እኛ ለፍቅራችን እንጂ ለጥላቻ ጊዜ የለንም ያሉ ሲሆን የግጭት ነጋዴዎች በፍፁም አዲስ አበባ ላይ ሊፈነጩ አይችሉም ብለዋል፡፡ አዲስ አበባ በዚህ በኩል ለየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ ምሳሌ ናት፡፡ ህዝቦቿ በፍቅር አብሮነት ያለምንም ልዩነት አብሮ በመኖር ምሳሌ ናቸው በማለት ከንቲባ አዳነች ተናግረዋል፡፡
ሕብረተሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን አዘውትረን ከመስራታችን ጎን ለጎን የመለያየት ነጋዴዎችን / የግጭት ጠማቂዎችን እምቢ ልንላቸው ይገባል ያሉ ሲሆን ይህ ደግሞ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ፤የአዲስ አበባ ልጆች ወጣቶች ሃላፊነት ነው በማለት አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡