‹‹እኛ ትግራውያን ኢትዮጵያዊ ነን!! ከመንግስት ጎን ሆነን የሀገር መከላከያ ሰራዊትን እንደግፋለን!!›› ሲሉ በክፍለ ከተማው የትግራይ ተወላጆች አስታወቁ።
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማው የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አድርገዋል።
የትግራይ ህዝብ ከህወሓት ጋር አንድ ነው ብሎ ማመን ትክክል አለመሆኑን ያስታወቁት ተወላጆቹ ሴቶች፣ህፃናትንና አረጋውያንን ለጦርነት ማግዶ ትግራይን ያለትውልድ አስቀርቷል በመሆኑም እኛ ትግራውያን ኢትዮጵያዊ ነን ከመንግስት ጎን ሆነን የሀገር መከላከያ ሰራዊትን እንደግፋለን ሲሉ አስታውቀው መንግስትም ጦርነቱን በፍጥነት ጨርሶ ወደ ስራ መግባት አለብን እኛም በሀገር ጉዳይ ላይ መሳተፍ እንፈልጋለን ሲሉ የውይይቱ ተሳታፊዎች ገልፀዋል።
አቶ ዘሚካኤል ኃይሉ የክፍለ ከተማው ፍትህ ፅህፈት ቤት ኃላፊ መድረኩ ባሉ ችግሮችና እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ለሀገር ሰላም የምናደርገውን አስተውፅኦ ለመነጋገር ነው ያሉ ሲሆን እኛ የትግራይ ተወላጆች አካባቢያችንን ከመጠበቅ፤ልጆቻችንና ወንድሞቻችን እኩይ ተግባራት ላይ እንዳይሳተፉ በጋራ መስራት አለብን፤አንገታችንን እንድንደፋ ያደረገንን ህወሓትን ልንቃወምና ልንታገል ይገባል በማልት አስታውቀዋል።