አለማቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለሴት አመራሮች የህይወት እና የስራ ተሞክሯቸውን ያካፈሉ ሲሆን ከሴቶች አመራሮችም እውቅና ተሰቷቸዋል ።አለማቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ሴት አመራሮች ከህይወት እና ከስራ ተሞክሮአችን እንድንማማር በተዘጋጀው ፕሮግራም እና ባልጠበኩት መንገድ ለለተሰጠኝ እውቅና፤ በጣም ላመሰግን እወዳለሁ ብለዋል ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ።
እውቅናው በይበልጥ ለመስራት የሚያበረታታ ነውና ከእኛ የሚጠበቀው ትጋት፣ በቅንነት እና በታማኝነት ማገልገል ነው ያሉት ወ/ሮ አዳነች በአመራር ላይ ያለን ሴቶች ያለን ስኬት የብዙ ሴቶች ልፋት፣ ትግል እና ተጋድሎ ውጤት እንደሆነም መገንዘብ ተገቢ መሆኑን ገልጸዋል ።ይህንን ያማረ እና አበረታች ፕሮግራም ያዘጋጁትን የአዲስ አበባ ሴት አመራሮችን እና አደረጃጀቶች ወደፊትም ብዙ አመራሮችን ለመፍጠር በበኩላችን በመልፋት እና በትጋት ምሳሌ ሆነን እንስራ ፤እላለሁ ሲሉ ተናግረዋል ።