በምስራቅ ታላቁን የናይል ወንዝ፤ በምዕራብ አመቱን ሙሉ የማይነጥፈዉን የኮንጎ ወንዝ በጉያዋ ይዛ የምትጠማ ፣ የምትራብ ፣ የምትታረዝ፤ የሌሎችን ቁራሽ የምትጠብቅ አህጉር ልትኖረን አይገባም ።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቲዉተር አካዉንታቸዉ ባስተላለፉት መልዕክት “የአፍሪካ ጊዜ አሁን ነው፣ አብረን ከድህነት ጉድጓድ በፍጥነት መውጣት እንችላለን ” የሚል መላው አፍሪካውያንና ትዉልደ አፍሪካውያንን ትኩረት ያደረገ መልእክት አስተላልፈዋል ።
በተጨማሪም “የአፍሪካ ጊዜ አሁን ነው አብረን ከድህነት ጉድጓድ ፣ አለመተማመን እና ክብርን ከመለመን በፍጥነት መውጣት እንችላለን” ነዉ ያሉት ።
“በኢኮኖሚ ውህደት፣ ሀብቶቻችንን እና እውቀታችንን በማጣመር አጀንዳ 2063 ን በጋራ ማሳካት እንችላለን” ሲሉ ገልጸዋል።
ባለፉት 3 አመታት የግጭትና የርሀብ ምሳሌ የነበረውን የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና በመደመር እሳቤ በኢኮኖሚ ፣ በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እሳቤዎች ለማስተሳሰር የተሄደበት ርቀትና የተገኘው አንፀባራቂ ዉጤት ለቀጠናው ብሎም ለመላው አፍሪካ ትልቅ መነቃቃትን ፈጥሯል።
የአህጉሩ ርዕሰ መዲና የሆነችው አዲስአበባም ከ1.3 ቢሊዮን በላይ የሆኑ የአህጉሩ ዜጎች የጋራ አጀንዳ የሆነዉን “አጀንዳ 2063” በሁለንተናዊ መልኩ እንዲሳካ ለማስቻል የሚጠበቅባትን ሁሉ ለማድረግ ከምንጊዜዉም በላይ ዝግጁ መሆኗን እገልፃለሁ ።
#አፍሪካ ትችላለች !!