ከዛሬ ሰኞ ህዳር 6 እስከ ህዳር 15 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የኮቪድ 19 ክትባት ዘመቻ እድሜው ከ12 ዓመት በላይ የሆኑ በአቅራቢያቸው በሚገኝ ጤና ጣቢያ በመሄድ ክትባቱን መውሰድ እንደሚችሉ የቢሮ ሃላፊው ዶክተር ዮሃነስ ጫላ አስታውቀዋል።
ከጤና ጣቢያዎች በተጨማሪም የክትባቱን ተደራሽነት ለማስፋት በትላልቅ የገበያ ቦታዎች ፣ ሞሎች ፣ በባንኮች ፤ በትራንሰፖርት መናህሪያዎች ፤ በኢንዱስትሪ ፓርክ እና በሌሎች በተመረጡ ቦታዎች ይሰጣል ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ እስከአሁን ከግማሽ ሚሊየን በላይ ነዋሪዎች የኮቪድ 19 ክትባት የተሰጠ ሲሆን ለ10 ቀናት በሚካሄደው የክትበት ዘመቻ ከ1 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ :: ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ የክትባት ቡድኖች መደራጀታቸውን ዶክተር ዮሃንስ ጫላ ገልጸዋል፡: