ማምሻችንን በልደታ ክ/ከተማ ምንም ገቢ ለሌላቸው እና ለተለያየ ማህበራዊ ችግር የተጋለጡ ዜጎቻችን የኑሮ ጫና ለማቃለል በማሰብ በተዘጋጀዉ ፕሮግራም ላይ ስለበጎነት ጥሪ ያደረግንላችሁ በክ/ከተማው የተለያየ ስራ ላይ የተሰማራችሁ ባለሃብቶች ፤ላደረጋችሁት አስተዋጽኦ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡
ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ የተገባውን ቃል በተግባር እንደምታውሉት እና በውጤቱም ለችግር የተጋለጡ ደጋፊ የሌላቸው ወገኖቻችንን በመደገፋችሁ በረከቱን ከፈጣሪ እንደምታገኙት እናምናለን፡፡
አገር የምትገነባው በታታሪዎችና በበጎ አሳቢዎች ጥረት ነው፤ ሁሌም እንደምንለው የዜጎቻችንን ህይወት የማይለዉጥ የአገር ግንባታ አይታሰብም።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!”
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ