የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እና የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የስራ ዕድልና ምግብ ዋስትና ዘርፍ አመራሮች በጋራ በመሆን የሴፍቲኔት ፕሮግራም ተጠቃሚዎችን ያሉበትን ሁኔታና የደረሱበት የኑሮ ደረጃ ጎበኙ።
ወ/ሮ ታዱ ብዙ የምትኖረው በጉሌሌ ክ/ከ ወረዳ 4 ሲሆን ሴፍቲኔት ተጠቃሚ መሆን የጀመረችው በ2011 ዓ.ም ነው። ይሁንና ፕሮጀክቱ በሚሰጣት ድጋፍ ከልመና ተነሰታ በግል ስራ ተሰማርታ እራሷንና ቤተሰቦቻን በማስተዳደር ጥሩ ህይወት መኖር እንደጀመረች በእንባ የታጀበ ደስታዋን አጋርታለች።
ሌላኛዋ የሴፍቲኔት ተጠቃሚ ወ/ሮ ወርቅነሽ አንሳ ስትሆን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ወረዳ 11 መኖሪያ ቤቷ ተገኝተን የደረሰችበትን የኑሮ ደረጃና ቃኝተናል። ይሁን እንጂ ፕሮጀክቱ በሚሰጣት ድጋፍ በአንድ በግ ከማርባት ጀምራ በአጭር ጊዜ ውስጥ 30 በጎችን ማርባት እንደቻለች ተናግራ በቀጣይም የእርባታ ቦታ ድጋፍ ቢደረግላት የተሻለ ደረጃ ላይ መድረስ እንደምትችል ገልፃለች።
ሚኒስትሯ ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ለሴፍቲኔት ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ለአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ የበዓል ሰጦታ በግ እና የልጆች የትምህርት ቤት ቁሳቁስ ያበረከቱ ሲሆን በጉሌሌ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ለምትኖር የሴፍቲኔት ፕሮግራም ተጠቃሚ ቀበሌ ከፈቀደ በቀጣይ ዓመት ቤቷን ሊሰሩላት ቃል ገብተዋል።
የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ፡ የስራ ዕድልና ምግብ ዋስትና ዘርፍ፡ የከተማ ምግብ ዋስትና እና ኑሮ ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጥላዬ አለማየሁ በበኩላችው የእርባታ ቦታ ድጋፍ በተመለከት በቀረበላቸው ጥያቄ ላይ ጉዳዩን ለሚለከተው አካል በማቅረብ ክትትል እንደሚያደርጉላቸው ምላሽ ሰተዋል።
በመጨረሻም ክብርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒና ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመተባበር ለሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች በቀጣይ የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍና ክትትል እንደሚድርጉላቸው ገልፀው ጉብኝቱ ተጠናቋል።