የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ንግግሩን የሚመሩ አካላትን፤ ቀንና ስፍራን አሳውቆ የሰላም ውይይቱ እንዲጀር በይፋ ጥሪ አቅርቧል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት ግብዣ መንግሥት ከዚህ በፊት ያቀረባቸውን አቋሞች የጠበቀ ሆኖ መገኘቱን አገልግሎቱ አስታወቋል።
ንግግሩ በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ብቻ እንዲሆንና ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲደረግ መንግሥት አቋሙን ሲገልጽ መቆቱንም አስታውሷል።
ግጭቱን ለመፍታት መንግሥት ሁሉንም ዓይነት የመፍትሔ እርምጃዎች ለመውሰድ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ያስታወሰው አገልግሎቱ ይህንኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጿል።