– የነባር 139,008 የ20/80 እና የ40/60 ቤቶች ፕሮግራም የተመረጡ ወደ ቤት ለመግባት የሚያስችሉ ስራዎችን በማጠናቀቅ አፈጻጸሙን 13ዐ, ዐዐዐ (98.65%) በማድረስ ባለእድለኞች ወደ ቤታቸው እንዲገቡ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡
– በከተማው በጀት ከሚገነቡት 1ዐ, ዐዐዐ የኪራይ ቤቶች ውስጥ 4, 4ዐዐ በሚቀጥለው መስከረም ወር የሚጠናቀቁ ሲሆን 5,6ዐዐ ተገጣጣሚ ቤቶች ደግሞ ግንባታ በአማካይ 29.25% ማድረስ ተችሏል፡፡
– በጋራ መኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር 4,940 ነዋሪዎች በ60 ማህበራት እንዲደራጁ ተደርጓል፡፡ ከዚህ ውስጥ የ54 ማህበራት ቦታ ተረክበው የመጀመሪያ ኘሮግራም ተካሄዷል፡፡
– በመንግስትና በግል አጋርነት የቤት ልማት ፕሮግራም የ60ሺህ ቤቶች ግንባታ ለማስጀመር ቅድመ ሁኔታን የማጠናቀቅ ስራ ተሰርቷል፡፡
– የ90 ቀናት ልዩ ዕቅድ በጎ ፈቃደኞች ባለሃብቶችን በማስተባበር እና በከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ ከ6,415 ቤቶችን በማስገንባት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የከተማችን ነዋሪዎች በኪራይ ለማስተላለፍ ተችሏል::
– በአጠቃላይ ለባለእድለኞች የተላለፉት 130 ሺህ ቤቶችን ለኪራይ ከተገነቡት 4,400 እና ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ላሉት ነዋሪዎች የተገነቡትን 6,415፣ በድምሩ 140,815 ቤቶችን ለነዋሪዎች ማቅረብ ተችሏል፡፡
All reactions:

Yenigatkokeb Ababu and 285 others