የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ /ቤት አዘጋጅነት በመካሄድ ላይ ባለው ውይይት እየተሳተፉ የሚገኙ አመራሮች እና ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የተውጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደጀንነታቸውን ለማሳየት ደም ልገሳ ለግሰዋል።
የኢትዮጵያን ህልውናና ሉዓላዊነት በማስከበር ላይ የሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ከሙያቸው ባለፈ በደም ልገሳ እና በሌሎች ተግባራት እገዛ እያደረግን ነው ያሉት ባለሙያዎቹ በቀጣይም የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።