መሰረታዊ የትራንስፖርት እንቅስቃሴን በማሳለጥ ፣ የትራፊክ ፍሰት ስርዓቱን በማዘመን ፣ በመንገድ ደህንነት ፣በወንጀል እንቅስቃሴ፣ በእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ፣የአምቡላንስ አገልግሎቱን ለማቀላጠፍና ለማዘመን አገልግሎቱን ከአንድ ማእከል መስጠት የሚያስችል ፣ ከመሬት ወለል በታች የተገነባ ባለአራት ወለል (G-4 )እጅግ ዘመናዊና የዘመኑን የእድገት ደረጃ የዋጀ ፕሮጀክት በመጠናቀቅ ሂደት ላይ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ ለግንባታው ወደ አንድ ቢሊዬን ብር እንዲሁም ለቴክኖሎጂ ገጠማ ደግሞ ወደ1 ቢሊዬን ወጪ የሚደረግበት ሲሆን የተጀመረውን አዲስ አበባን በሁሉም መስክ ስማርት ሲቲ (Smart City) በማድረግ በኩል አይነተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በፍጥነት እዚህ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ላደረጋችሁ አካላት ሁሉ በራሴና በከተማችን ነዋሪ ስም አመሰግናለሁ!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!”
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ