አዲስ አበባ ያሏትን ሃብቶች በመጠቀም እንደ ስሟ ውብ እና አበባ የማድረግ ስራችን አካል የሆነው ይህ ዊንዶ ኦፍ አፍሪካ ፕሮጀክት በ84 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ሲሆን በውስጡ እኛነታችንን ባህላችንን የምናንፀባርቅበት ግዙፍ የአፍሪካ ሙዚየም ፣የአረንጏዴ ቦታዎች፣ የውሃ የመዝናኛ ቦታዎች ፣የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች ፣ሰው ሰራሽ ሃይቆች ፣ የእንግዳ ማረፊያዎችና የግብይት ሞሎች እንዲሁም የህፃናት መጫወቻ ስፍራዎች ተካተውበታል::
ይህ ፕሮጀክት ግንባታው በመንግስት በጀት ብቻ ሳይሆን በርካታ ባለሃብቶች በአጋርነት ተባብረው የሚገነቡት ሲሆን ለከተማችን ተጨማሪ መስህብ ፣የገቢ እድገትና ሰፋ ያለ የስራ እድልን የሚፈጥር ይሆናል::
ከንቲባ አዳነች አቤቤ