ከተማዋን ውብ እና ፅዱ ለማድረግ የከተማው ነዋሪ በፅዳት እና ውበት ስራ ባለቤት በመሆን መሳተፍ እንዳለበት በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ አሳስበዋል።
አቶ ጥራቱ በየነ፣ የየካ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መራጊያው ተበጀን ጨምሮ ሌሎች የከተማና የክ/ከተማ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች፣ የወረዳ 12 ነዎሪዎች እና የፀጥታ አካላት በፅዳት ንቅናቄ ዘመቻ ተሳትፈዋል።
አዲስ አበባን ውብ እና ፅዱ ለማድረግ አካባቢን በማፅዳት የተጀመረው በትምህርት፣ በተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማትን የማፅዳት ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን በንቅናቄ ዘመቻው ተገልፆል።
በከተማዋ የሚስተዋለውን የፅዳት ሁኔታ ለመቀየር በህብረተሰቡ ትብብር ለውጥ እንደሚመጣ አቶ ጥራቱ መልዕክት አስተላልፈዋል።