ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በጉምሩክ ኮሚሽን 27 መኖርያ ቤትና 8 የንግድ ቤቶችን ፤በመከላከያ ኢንተርፕራይዝ የተገነቡ 8 ቤቶችን፤ እንዲሁም በሄኒከን ቢራ የተገነቡ 50 ቤቶችን በድምሩ 103 ቤቶችን ለአቅመ ደካሞች አስረከቡ
ከንቲባ አዳነች በርክብክብ ስነስርዓቱ የነዋሪዎችን ችግር መቅረፍ የሚችሉ ስራዎች በመስራታቸው ደስተኛ እንደሆኑ ገልፀው ስለወገኖቻቸው ህመም የሚያስቡ በጎ ፍቃደኞች ስለበዙ የቂርቆስን ጨምሮ ከ952 በላይ ቤቶችን በዛሬው ዕለት ብቻ አስረክበናል ብለዋል።
ይህ የሚያሳየው ከተባበርን ከተባበርን፣ ከተደማመጥን፣ከተጋን፣አቅማችን ከዚህ በላይ መሆኑን ነው ያሉት ከንቲባዋ አመራሮቻችንም ሆነ በጎ ፍቃደኞች በርቱልን የምናርፈው ስንበለፅግ ብቻ ነው ብለዋል
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ አንዱ ተግባር ቤቶችን ለህብረተሰቡ ገንብቶ ማስረከብ መሆኑን ገልፀው በዛሬው ሳናበቃ በቀጣይም የነዋሪዎቻችንን ምቾት ለመጠበቅ ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል