ቀልፉ ባስረከቡበት ወቅት ከንቲባ አዳነች እንደተናገሩት እንደ መንግስት የነደፍነውኖ ሰው ተኮር ዕቅዳችንን ማዕከል በማድረግ በ2014 ዓ.ም በአጠቃላይ ስምንት ሺ ቤቶችን ገምብተን ድጋፍ ለሚሹ አቅመ ደካማ ወገኖች አስረክበናል ብለዋል
ባለፉት ግዚያት በዓመት የነበረው ከፍተኛ ቤት የመገንባት አሃዝ ሶስት ሺ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች ከበጎ ፈቃደኞችና ከአገር ወዳድ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ከሚወጡ አካላት ጋር ከተቀናጀን ብዙ መሥራት እንደምንችል የተማርንበትም ምዕራፍ ነው ብለዋል
በዛሬው ዕለት ዘጠኝ መቶ 52 ቤቶችን ከበጎ ፈቃደኛች ጋር በቅንጅት ግንባታቸውን አጠናቀን ሙሉ በሙሉ እርክክብ እንፈጽማለን ያሉት ከንቲባ አዳነች ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ የሚወጡ ዜጎች በሚፈለገው ልክ ከደገፉን ብዙ በመሥራት ለአገር በጎብዝናቸው ወራት እጅግ የደከሙ አቅም ደካማ ወገኖቻችን መደገፍ እንችላለን ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል
ከተባበርንና በቅንጅት የየድርሻችንን ኃላፊነት ወስደን ከሰራን ከዚህ በላይ ማሳካት እንችላለን ያሉት ከንቲባ አዳነች አሁን በምንገኝበት ወቅት በጎ ፈቃደኝነት ባህል ልሆን ይገባል ብለዋል
የናንተን እምባ ማበስና የኑሮ ጫና ማቃለል የመንግስታችን ቀዳሚ ኃላፊነት ነው ያሉት ከንቲባዋ በዘላቂነት ተመሣሣይ ችግር ያለባቸውን ወገኖች ለመርዳት ከተማ አስተዳደሩ ከበጎ ፈቃደኞችን ጋር ይሰራል ብለዋል ከንቲባዋ
የበለጠ እያሰፋን እንድንሰራ የእስካሁኑ የአቅመ ደካማ ወጎኖች ቤት ግንባታ ምሳሌ ሆኖናል ያሉት ከንቲባዋ የምናርፈው በሁሉም ረገድ ሁለንተናዊ ብልጽግናችንን ስናረጋግጥ ብቻ ነው ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል