1. ጤናን በተመለከተ
– የጤና አገልግሎት ተደራሽነቱንና ጥራቱን ለማሳደግ በግንባታ ላይ ካሉ ፕሮጀክቶች ውስጥ የ28 የጤና ኘሮጀክቶች ግንባታ የተጠናቀቀ ሲሆን የቀሩት 3 ሆስፒታሎችን ጨምሮ ሌሎች ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው የግንባታ ጊዜ መሰረት እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
– የከተማ አስተዳደሩ በበጀት ዓመቱ ለጤና መድህን 3ዐዐ,ዐዐዐ,500 ብር ደጉሟል፡፡
– ከፍለው መታከም ለማይችሉ የኩላሊት ታካሚዎች ከተማ አስተዳደሩ ከ2ዐሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ በመፈፀም ነፃ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
2. የተማሪ ምገባን በተመለከተ
– ለ700 ሺህ ተማሪዎች በቀን ሁለቴ ከመመገብ፣ የተማሪ ዩኒፎርም፤ ደብተር እና የመምህራን ጋዋን ማሰራጨት ተችሏል፡፡
– የምገባ ፕሮግራማችን የተማሪዎችን የመማር ብቃትና ተሳትፎ ከማሳደጉም በላይ ከተማችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሀገራችን እውቅና እንድታገኝ ያስቻለ መልካም ተግባር ሆኗል፡፡
3. ገቢን በተመለከተ
– ገቢ ከማሳደግ አንጻር በአስራ አንድ ወራት 1ዐዐ ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ1ዐ4 ቢሊዮን ብር በላይ (1ዐ4% በላይ) መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን አፈፃፀሙ ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ4ዐ ቢሊዮን ብር ብልጫ ወይም 49 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡
– የገቢ አሰባሰቡን በማሻሻል በተለያየ ምክንያት ቆመው የነበሩ 19 ፕሮጀክቶችን ለማስጀመር የተቻለ ሲሆን፣ ለ22 ወራት ስራ ያልነበራቸው ከ150 በላይ የኮንስትራክሽን ማህበራት ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡
4. የስራ ዕድል ፈጠራን በተመለከተ
– ለ464,310 ስራ ፈላጊዎች የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ 416,999 (90%) መፍጠር ተችሏል፡፡
– ለ1,544 ነባር አምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት ሂደታቸውን በማስቀጠል የገቢ ምርትን መተካታቸውን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
5. የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራን በተመለከተ፡-
– 6,415 የአቅመ ደካሞች፣ የአረጋውያንንና የሀገር ባለውለታዎች ቤቶች የተገነቡ ሲሆን በዚህ ድጋፍ 33,500 ቤተሠቦችን ተጠቃሚ ሆነዋል።
– ከበጎ አድራጊ አካላት 3 ቢሊየን የሚደርስ ሀብት በማሰባሰብ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ 620,037 ህብረተሰብ ክፍሎች በበዓላትና በተለያዩ ጊዜያት ማዕድ ለማጋራት ታቅዶ ለ867,389 ነዋሪዎችን ማዕድ ማጋራት ተችሏል፡፡
– በሰው ተኮር እና በጎፈቃድ ስራ 6 ቢሊዮን ብር የሚገመት የበጎፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ 7.3 ቢሊዮን ብር የሚገመት የበጎፈቃድ ተግባራት በማከናወን 1.1ሚሊዮን የከተማችን ነዋሪዎች በቀጥታ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።