በ2015 በጀት ዓመት የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራ መከናወኑን ከንቲባ አዳነች ገልፀዋል።
በሪፖርታቸው ያነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች፤ (በሰላምና ፀጥታ በተመለከተ ያነሱት )

በሰላም፤ አብሮነትና ወንድማማችነት/ እህትማማችነትን በሚያጠናክሩ ጉዳዩች ውጤታማ ሥራዎች መሠራታቸውን

ጠላት አዲስ አበባን ሌላው ዋነኛው ግንባር በማድረግ ህዝባዊና የሃይማኖት በዓላትን ለማወክ ከፍተኛ ዝግጅት ቢያደርግም መዋቅራችንን፣ መላ ህዝባችንን፣ የፀጥታ ሃይሉንና የተለያዩ አደረጃጀቶችን አቀናጅተን በመምራታችን የጠላትን እቅድ ማክሸፍ መቻሉን

1.5 ሚሊዩን ህዝባችን አካባቢውን እንደጠብቅ በማነቃነቅና በማደራጀት የሰላም ሰራዊቱ፤ የደንብ ማስከበር፤ የፖሊስ ሃይላችን ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር የከተማችንን ሰላምና ጸጥታ ማስፈን መቻሉ

ከወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ አኳያ በቀጣይም የሀገር ሉዓላዊነትና ግዛት አንድነት ለማረጋገጥ የሚያግዝ የደጀንነት ስራችንን በማጠናር ለሶስተኛ ዙር 486.2 ሚሊዮን ብር የሚገምት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ መደረጉን :

ለዘመናት የተንከባለለና ሳይቋጭ የግጭት፤ መፈናቀልና የፖለቲካ አጀንዳ ሆኖ የኖረው የአዲስ አበባ እና አጎራባች ፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የአስተዳደር ወሰን ህገ-መንግስቱንና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋራ በተቋቋሙ ኮሚቴዎች እና በፌዴራል መንግስት የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እልባት በመስጠት ታሪካዊና ውጤታማ ስራ መስራት ተችሏል፡፡