በውይይቱ ላይ በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡ መሆኑን ነዋሪዎቹ ገልፀው በቀጣይ የከተማ አስተዳደሩን ትኩረት በሚፈልጉ ጉድለቶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጏል::
ከነዋሪዎቹ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ህዝባችን በሰጠን አደራ ልክ ከተማዋን የሚመጥን አስተሳሰብ በማሰረፅ ፅንፈኝነት ፥ ጥላቻ ፥ ህዝብን የሚከፋፍሉ ሃሳቦችን መዋጋት አለብን ብለዋል::
የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመመለስ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ነዋሪዎችን የኑሮ ጫና መቀነስ እና የሚደግፉ ፕሮጀክቶችን ማስፋፋት አለብን ያሉት ከንቲባ አዳነች ከህዝቡ ለሚነሱ ጥያቄዎች እና ቅሬታዎች ተገቢውን መልስ እንሰጣለን ብለዋል::