በውይይታቸውም በሁለቱ እህት ከተሞች መካከል በተደረሰው ስምምነት መሰረት የከንቲባ ነፃ የትምህርት እድል ፕሮግራም (Mayor’s Scholarship Program) ማመቻቸት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን የKNU ዩኒቨርስቲ መስፈርት ለሚያሟሉና የተሻለ ውጤት ለሚያስመዘግቡ የአዲስ አበባ ተማሪዎች በከንቲባ የተሰየመ ነፃ የትምህርት እድል ለመስጠት ተስማምቷል::
የከንቲባ ነፃ የትምህርት እድል (Mayor’s Scholarship program) የከተማ አስተዳደሩ የአዲስ አበባ እህት ከተሞች ውስጥ ከሚገኙ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር በከተማችን ለሚገኙ በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት ለሚያስመዘግቡ ተማሪዎች የነፃ የትምህርት እድል ለመስጠት በከንቲባ አዳነች አቤቤ የተጀመረ እንቅስቃሴ ሲሆን ለከተማችን ተማሪዎች መልካም እድል የሚፈጥር ይሆናል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሁለቱን ከተሞች የረዥም ዘመን ወዳጅነትን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመ የደቡብ ኮርያ ቹንቾን ከተማ ስኬታማ የስራ ጉብኝታቸውን አጠናቅቀው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል::