ከዚህ በፊት ለአካባቢው ነዋሪዎች በተገባው ቃል መሰረት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን በመለየት በዛሬው ዕለት የተለያዩ ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጀምሯል::
ከነዚህም መካከል:-
– በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎች ማቋቋሚያ የሚሆን ባለ 10 ወለል የመኖሪያ ህንፃ ግንባታ (በከተማ አስተዳደሩ የሚገነባ)
– በእንጨት ለቀማ ለሚተዳደሩ እናቶች የሚውል የእንጀራ መጋገሪያ ፋብሪካ
– ሁለት ባለ 12 ወለል የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ (በ70/30 ፕሮግራም የሚገነባ)
– ባለ አራት ወለል የስራ እድል ፈጠራ ሼዶች
– የተስፋ ብርሃን የማህበረሰብ የምገባ ማዕከል ግንባታን ጨምሮ የተለያዩ ፕሮጀክቶች በዛሬው ዕለት ግንባታቸው ተጀምሯል::
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች የተጀመሩት ፕሮጀክቶች እንጨት ለቅመው በጽናትና በትጋት ልጆቻቸውን ለሚያሳድጉ እናቶች እና የመስሪያ ቦታ ችግር ያለባቸው ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ እና በክፍለ ከተማው ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግር የሚያቀሉ ናቸው ብለዋል::
የከተማችን እድገትና ልምላሜ የሚረጋገጠው በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች እኩል ተጠቃሚ ሲሆኑ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች በቅርበት ክትትል በማድረግ እና ፕሮጀክቶቹን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለህብርተሰቡ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ እናደርጋለንም ብለዋል::