በጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተደረገው የ”ትምህርት ለትውልድ ” ጥሪ መሰረት በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ለማሻሻል የንቅናቄ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች የፌደራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል።
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትውልድ በእውቀትና በስነ ምግባር የሚታነጽባቸውን ትምህርት ቤቶችን ብቁ ለማድረግ እየሰራቸው ካሉ በርካታ ስራዎች መካከል በትምህርት ስራው ላይ ማኅበረሰቡን በንቃት የማሳተፍ ስራ አካል የሆነው ይህ ንቅናቄ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ሲሆን ዜጎችን ከተማሩባቸው ትምህርት ቤቶች ጋር በማገናኘት ትምህርት ቤቶቹን በቁሳቁስ፣ በዕውቀትና በገንዘብ በመደገፍ ለመማር ማስተማር የተመቸ ለማድረግ የተጀመረ ስራ ነው፡፡
በንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ትውልድ ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት የማያረጅ ኢንቨስትመንት ነው ያሉ ሲሆን የነገ ሃገር ተረካቢዎችን በማብቃት ረገድ የመማሪያ ቦታዎችን ለመማር ማስተማር ስራ ምቹ ለማድረግ ሁሉም የበኩሉን አስተዋፅዖ እንዲወጣ ጥሪ አስተላልፈዋል::
በመርሃ ግብሩ ላይ ትምህርት ቤቶችን እንዲያድሱ ለከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣ ለመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ፣ ለቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ እንዲሁም ለሌሎች የፌዴራል እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተለያዩ ክፍለከተሞች የሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶችን የመሰረተ ልማት እንዲያለሙ በአደራ ተሰጥቷቸዋል::
+12
All reactions:

176