ህንጻው ከንቲባ አዳነች የኦሮሚያ ልማት ማህበር ዋና ዳይሬክተር በነበሩበት ወቅት ያስጀመሩት ሲሆን የልማት ማኅበሩ ሕዝቡን እና ሃብትን በማስተባበር ያስገነባው ነው::
በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የኦሮሚያ ልማት ማህበት በሀገር አቀፍ ደረጃ ተማሪዎችን በእውቀትና በስነ ምግባር አንጸው በማስተማር ትልቅ ስም እና ዝና ያተረፉትን የኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በርካታ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን ፣የወጣቶች ስብዕና ግንባታ እና የሴቶችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ በርካታ የልማት ስራዎችን ሲሰራ የቆየ መሆኑን ጠቅሰው አንግቦ የተነሳውን ዓላማ ለማሳካት የሚያስችለውን ተጨማሪ አቅም የሚፈጥርለትን ሁለገብ ሕንጻ በአዳማ አስገንብቶ ለዚህ በማብቃቱ መደሰታቸውን ገልፀዋል::
በምርቃት መርሃግብሩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የኦሮሚያ ምክትል ፕረዝዳንት አቶ አወሉ አብዲ ፣ የኦሮሚያ ልማት ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አባዱላ ገመዳ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል::