ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማችን አዲስ አበባ ሰላም እና አብሮነት እንዲጎለብት ፣ በተለያዩ ሰው ተኮር ስራዎች አመራሩንና ህዝቡን በማስተባበር ዝቅ ብለው የነዋሪውን ጥያቄ ለመመለስ እያደረጉት ላለው ተግባር እና ከሁሉም የሃይማኖር ተቋማት ጋር በቅርበት ፣ በእኩልነትና በፍትሃዊነት በመስራት ላሳዩት ቁርጠኝነት የአዲስ አበባ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ቦርድ እውቅና ሰጥቷቸዋል::
በእውቅና መርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለሰጣቸው እውቅና ምስጋናቸውን አቅርበዋል::