የልህቀት ማዕከሉ የዶሮና የወተት ላም እርባታ፣ የከብት ማደለብ፣ የመኖ ማቀነባበሪያና የምርት ማሳያና መሸጫ ቦታዎችን ያካተተ ነው፡፡
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስተዳደራችን የነዋሪውን የኑሮ ጫና የሚያቀሉ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በከተማዋ ያለውን የዋጋ ንረት ለማርገብ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ ይገኛል ያሉ ሲሆን አሁን የተመረቀው ማዕከል በዘርፉ የሚሰማሩ 485 የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን የእውቀት፣ የክህሎት፣ የምርምር፣ የግብዓት፣ እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ምንጭ ሆኖ ያገለግላል ብለዋል::