የምርት ገበያው ሱቆችን ጨምሮ መጋዘን ፣ ወፍጮ ቤት እንዲሁም ልዩ ልዩ አገልግሎት የሚሰጡ ማዕከላት የተካተቱበት ሲሆን ለበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች ፣ አምራቾች እና አርሶአደሮች የስራ እድል የሚፈጥር ይሆናል::
በምርቃት መርሃ ግብሩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ፣ የፌደራል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ የከተማ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል::