ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ በጦር ሃይሎች ሆስፒታል ተገኝተው የሰራዊቱ አባላት ጎብኝተው የተለያዩ ድጋፎችን ና የምሳ ግብዣ አድርገዋል፡፡
በዚሁ ወቅት ከንቲባዋ እንደተናገሩት ‹‹በእናንተ መሃል ተገኝቶ በዓልን ማሳለፍ ከክብርም በላይ ክብር ነው፤ እናንተ የአገራችን ጀግኖች የአገራችን አርማ ናችሁ!! ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በገጠማት ፈተናዎች ሁሉ ፀንታ መሻገር እንድትችል ከስጦታ ሁሉ በላይ የሆነውን ስጦታ በመስጠት ሃገራችሁን ያፀናችሁ በመሆናችሁ ከእናንተ ጋር መሆን በእጅጉ ያስደስተናል ሲሉም ጨምረዋል፡፡
ድጋፉን የተቀበሉት ብ/ጀነራል ሃይሉ እንደሻው የጦር ሃይሎች ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አዛዥ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ ሆስፒታሉ አቅሙ እንዲጠናከርና አገልግሎቱን እንዲያሰፋ ለማድረግ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡