በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተቋሙ በ1935 ዓ/ም ለ18 ተጋቢዎች የጋብቻ ሁነትን ብቻ በመመዝገብ አገልግሎቱን የጀመረ መሆኑን ጠቅሰው ዛሬ ላይ ግን ቀልጣፋ እና ዘመናዊ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎቶችን እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቀት በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶች ዘምነው እና ዲጂታላይዝድ ሆነው የሚሰጡትን አገልግሎቶች ሁሉ ከአንድ ማዕከል በማድረግ እና መረጃ መያዝ የሚቻልበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውንም ከንቲባ አዳነች ተናግረዋል::