በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች ህጻናት ከጽንስ ጀምሮ ተገቢውን እንክብካቤ አግኝተው በአካልና አዕምሮ በልፅገው እንዲያድጉ የከተማ አስተዳደሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ያሉ ሲሆን የእናቶችን የኑሮ ጫና ማቅለል የሚያስችል የሕጻናት ማቆያ እና የሕፃናቱን ጤንነት ለመከታተል የከተማ አስተዳደሩ የህፃናት ክሊኒክ መገንባቱንም ገልጸዋል::
በሚቀጥሉት ሦስት አመታት 1000 ተጨማሪ የህፃናት ማቆያ ማዕከላት እንደሚገነቡ የገለፁት ከንቲባ አዳነች በህጻናት አስተዳደግ ዙሪያ የቤት ለቤት የግንዛቤ ማስጭበጫ ስራ የሚሰሩ 1400 ባለሙያውዎች በዛሬው ዕለት መመረቃቸውንም ጠቅሰዋል::