በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የምናጋራው ማዕድ ዱቄትና ዘይት ብቻ ሳይሆን በዚያ ውስጥ መተሳሰብና እና መረዳዳትን ከሁሉ በላይ ደግሞ ለዜጎቻችን ያለንን ፍቅር በተግባር የምናሳይበት ነው ብለዋል፡፡
በቀጣይም በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ማዕድ የምናጋራ ይሆናል ያሉት ከንቲባ አዳነች መተሳሰብ ማለት ካለን ማካፈል መሆኑን ላስተማሩን እና ከ1600 በላይ ካርቶን ቴምር ላበረከቱልን የበጎነትና የስራ ተምሳሌታችን የሆኑትን ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድን በከተማችን ነዋሪዎች ስም እናመሰግናለን ብለዋል::
ለነዋሪዎቹ የዘይት ፣ የምግብ ዱቄት እና የቴምር ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ዛቢሎን እና ሆራ ትሬዲንግ ላደረጉት አስተዋፅዖ ከንቲባ አዳነች አመስግነዋል::