በቁልፍ ርክክቡ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወንዝ ዳርቻ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎችን የጎርፍ አደጋ ተጋላጭነትን ለመቅረፍ እና በተበከሉ አካባቢዎች መኖር የሚያስከትልባቸውን ችግር ለመፍታት ነዋሪዎችን ከወንዝ ዳርቻ በማንሳት የተሻለ ንፁህ ቤት እየሰጠን የአዲስ አበባን ወንዝ ዳርቻዎች በማልማት ተወዳዳሪና የቱሪስት መዳረሻ ከተማ ለማድረግ እየሰራን እንገኛለን ብለዋል::
በሌላ በኩል ባንድ ወቅት በስራዎቻቸው ወገኖቻቸውን ሲያገለግሉ የነበሩ የዛሬ የቤት እድለኞች በጤና መጓደል እና በማህበራዊ ችግሮች ውስጥ ከነበሩት በማንሳት ቤት እንዲኖራቸው አድርገናል ያሉት ከንቲባ አዳነች በዛሬው ዕለት በአጠቃላይ ለ 200 አባወራዎች የመኖሪያ ቤት አስረክበናል ብለዋል::
በከተማዋ የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመቅረፍም መንግስት ከሚያደርጋቸው ጥረቶች ባሻገር የግል ባለሀብቱ አወንታዊ ሚና መጫወት የሚያስችለውን አሰራር በመቀየስ የ120 ሺህ ቤቶች ግንባታ ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑን አክለው የገለጹት ከንቲባ አዳነች ከተባበርንና ከተጋገዝን ከችግሮቻችን በላይ በመሆን ከተማዋን እንደስሟ ውብ እና ታላቅ የቱሪስት መዳረሻ ማድረግ እንችላለን ብለዋል፡፡
በለሚ ኩራ ከተካሄደው የመኖሪያ ቤት ቁልፍ ርክክብ በተጨማሪ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ማዕድ አጋርተዋል