የሸክላ እና የሽመና ውጤቶችን ወደ ውጭ ሀገር የሚልከው ሙያ ኢትዮጵያ፣ ለበርካታ የዕደ-ጥበብ ባለሙያዎች የስራ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ የውጭ ምንዛሬ ለሀገራችን ማስገኘት የቻለ ማህበር ነው።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጉብኝታቸው ወቅት ከተማ አስተዳደሩ በጥበበኛ እጆች የሚሰሩ መሰል የዕደ-ጥበብ ስራዎችን ያበረታታል፣ ድጋፍ ያደርጋልም ብለዋል።
የሙያ ኢትዮጵያ ባለቤት፣ ስራ አስኪያጅና ዲዛይነር ወይዘሮ ሳራ አበራ በበኩላቸው፣ ለጥበበኞች ልዩ ስልጠና በመስጠት የስራ ዕድል በመፍጠሬ ከማገኘው ገቢ የበለጠ ያስደስተኛል በማለት ገልፀዋል።