ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የከንቲባ ፅ/ቤት ሠራተኞች ለአዲስ ዓመት የማዕድ ማጋራት አከናወኑ፡፡
በትናንትናው እለት የዋለውን የበጎ ፈቃድ ቀንን ምክንያት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በፅ/ቤታቸው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ሰራተኞች የአመት በአል መዋያ የማእድ ማጋራት አከናውነዋል፡፡
ሰራተኞቹንም በርትተው እንዲሰሩና ለውጤት እንዲተጉ አበረታተዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የአዲስ አበባ ወጣቶች ሊግ ያሰባሰቡት ለአዲሱ አመት ለተማሪዎች ከ5 መቶ ሺህ ብር በላይ የሚገመት የመማሪያ ደብተር ድጋፍ ተደርጓል።