የሚገነቡ ሱቆቹና የመኖሪያ ቤቶች ወጣቶችንና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ያደርጋሉ ተብሏል።
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት በከተማችን የህብረተሰቡን ተስፋ የሚያለመልሙ ፕሮጀክቶችን እያከናወን ነው።የምንስራቸው የልማት ስራዎች አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ገልፀው ለሚሰሩ የልማት ስራዎች የባለሃብቶች ተሳትፎ የላቀ ነው ብለዋል። ማደግና መበልፀግ የሚቻለው ማህበረሰቡ አቅፎ በመሄድ ስራዎችን በመደጋገፍና በመተባበር መስራት ሲቻል ብቻ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
በልደታ ክ/ከተማ 200 በላይ የደሃ ቤቶችን፤ሁለት የምገባ ማዕከል ና ሁለት ዳቦ ፋብሪካዎችን እየተሰሩ ይገኛሉ ሲሉም ገልፀዋል።
ከተባበርንና በጋራ ከቆምን የማንለወጥበት ሁኔታ የለም ያሉት ከንቲባዋ ያለ እረፍት በመስራት ወደ ሌሎች ቦታዎች ሞዴል ሁኖ የሚሰፋ ስራ እንድንሰራ የማህበረሰቡ ቀጣይነት ያለው ትብብር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሰግደው ሀ/ጊዮርጊስ በበኩላቸው ፈርሰው የሚገነቡ ቤቶች ለመኖሪያ ምቹ ያልሆኑ ናቸው ያሉት አቶ አሰግደው ግንባታው ሲጠናቀቅ የክ/ከተማዋን ገፅታ በመገንባት ረገድ ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።
የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስራ አስኪያጅ አቶ ጀማል በበኩላቸው በድሀ ተኮር የስራ እንቅስቃሴዎች ላይ በመሳተፍ ማህበራዊ ኃላፊነታችንን እንወጣለን ሲሉ ገልፀዋል።