ዛሬ ማለዳ በአዲስ አበባ እየተገነቡ ያሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ያሉበት ደረጃ ፤ተዘዋውረው የጎበኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፕሮጀክቶቹ በታሰበላቸው ጊዜ በፍጥነት እንዲሁም ጥራታቸውን ጠብቀው ስለሚጠናቀቁበት ሁኔታ ከየፕሮጀክቶቹ የስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች ጋር ተነጋግረዋል፡፡
ተዘዋውረው ከተመለከቷቸው ፕሮጀክት መሃከል የአፍሪካ ኢኖቬሽን ማእከል፤ የአዲስ አበባ ዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ፤ የታላቁ የቅርስና የመኪና ማቆምያ ፕሮጀክትና የካ ቁጥር ሁለት መኪና ማቆምያ ይገኙበታል፡፡
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፕሮጄክቶቹ የገጠማቸውን የሲሚንቶና የውጪ ምንዛሬ እጥረት በመቅረፍ ጥራታቸውን ጠብቀው በብቃት የመጨረስ አቅም ማሳደግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡