ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬው እለት በ60 ቀናት እቅድ አካል የሆነውንና በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን በየካ ክ/ከተማ የተቋቋመውን 200 ዜጎች በቀን የሚመግበውን የምገባ ማእከል መርቀው ከፍተዋል፡፡
በምርጫ ስንወዳደር ፓርቲያችን ሰው ተኮር ነው ብለን ነበር ያሉት ከንቲባዋ በሚሰራውና ባገኘነው ሃብት ሁሉ ቅድሚያ ለሰው ነው በማለት መጀመርያ ለሰው የሚሆን ነገር ሳይሰራ አገር እቀይራለሁ ሊል አይችልም ሲሉ ገልፀዋል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ማእከሉን በመረቁበት ወቅት በሰጡት አስተያየት፡፡
እናንተ በቀን አንድ ጊዜ ለመመገብ በምትቸገሩበት አካባቢ እኛ በቀን ሶስት ጊዜ እየበላን መቀጠል የለብንም በማለት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የምገባ ማእከሉን በመክፈቱ ሊመሰገን እንደሚገባ ከንቲባ አዳነች አውስተው እዚ ስንኖር ለአካባቢው ህብረተሰብ መልካም በረከት መሆን አለበት በማለት ገልፀዋል፡፡
ሁሉም ሲተባበር ፤ሁሉም ሃላፊነቱን ሲወጣ ፤ በየአካባቢው ወገኖቹን ሲያስብ ነው ኢትዮጵያ የምትቀየረው ያሉት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች በከተማች ብዙ መስርያ ቤቶች አሉ፤ የከተማውን ህዝብ ጫና ማቃለል ያለባቸው ፤ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ድርጅት መማር አለባቸው ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ከዚህ በፊት የምገባ ማእካት ስራ ሲጀመር አንዱን ማእከል በነፃ በመገንባት አስተዋፅኦ ማበርከቱን ከንቲባ አዳነች አውስተዋል፡፡
እንዲሁም ዛሬ የተመረቀው ምገባ ማእከል ቋሚ ወጪ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሰራተኞችና ሃላፊዎች የወር ደሞዝ መዋጮ የሚቀጥል ይሆናል